በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“በአምላክ ቤት ሥራ ጣልቃ አትግቡ”

“በአምላክ ቤት ሥራ ጣልቃ አትግቡ”

እገዳ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም ሊቀ ካህናቱ የሆሹዋ (ኢያሱ) እና ገዢው ዘሩባቤል ቤተ መቅደሱን መልሶ የመገንባቱን ሥራ በግንባር ቀደምትነት ይመሩ ነበር (ዕዝራ 5:1, 2w22.03 18 አን. 13)

ተቃዋሚዎች ሥራው እንዲካሄድ የፈቀደው ማን እንደሆነ በጠየቁበት ጊዜ አይሁዳውያኑ ቂሮስ ያወጣውን አዋጅ ጠቀሱ (ዕዝራ 5:3, 17w86 2/1 29 ሣጥን አን. 2-3)

ንጉሡ፣ አዋጁ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋገጠ ከመሆኑም ሌላ ተቃዋሚዎቹ በሥራው ላይ ጣልቃ መግባታቸውን እንዲያቆሙ አዘዛቸው (ዕዝራ 6:7, 8w22.03 15 አን. 7)

ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ይህ ዘገባ ይሖዋ ሥራውን እንዲመሩ የሾማቸው ሰዎች የሚሰጡንን መመሪያ ሙሉ በሙሉ መረዳት በሚከብደን ጊዜ መመሪያውን እንድንከተል የሚያነሳሳን እንዴት ነው?—w22.03 19 አን. 16