ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለቤተሰባችሁ ደስታ አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላላችሁ
ይሖዋ ቤተሰቦች ደስተኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል። (መዝ 127:3-5፤ መክ 9:9፤ 11:9) ይሁንና በዚህ ዓለም ውስጥ ያለው ውጥረት እንዲሁም የቤተሰባችን አባላት የሚሠሩት ስህተት ደስታችንን ሊያደፈርሰው ይችላል። ታዲያ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለቤተሰቡ ደስታ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንዴት ነው?
ባል ሚስቱን ሊያከብራት ይገባል። (1ጴጥ 3:7) ከእሷ ጋር ጊዜ ያሳልፋል። ከእሷ በሚጠብቀው ነገር ረገድ ሚዛናዊ ነው፤ እንዲሁም ለእሱና ለቤተሰቡ ለምታደርገው ነገር ያደንቃታል። (ቆላ 3:15) ፍቅሩን ይገልጽላታል፤ እንዲሁም ያሞግሳታል።—ምሳሌ 31:28, 31
ሚስት ደግሞ ባሏን በተለያዩ መንገዶች ትደግፋለች። (ምሳሌ 31:12) ትገዛለታለች፤ እንዲሁም ትተባበረዋለች። (ቆላ 3:18) እሱን ስታነጋግርም ሆነ ስለ እሱ ስትናገር ደግነት ታሳያለች።—ምሳሌ 31:26
ወላጆች ለልጆቻቸው ጊዜያቸውን ይሰጣሉ። (ዘዳ 6:6, 7) እንደሚወዷቸው ይነግሯቸዋል። (ማቴ 3:17) ለልጆቻቸው ተግሣጽ የሚሰጡት በፍቅርና በማስተዋል ነው።—ኤፌ 6:4
ልጆች ወላጆቻቸውን ያከብራሉ፤ እንዲሁም ይታዘዙላቸዋል። (ምሳሌ 23:22) የሚያስቡትንና የሚሰማቸውን ለወላጆቻቸው ይናገራሉ። ወላጆቻቸው የሚሰጧቸውን ተግሣጽ ይቀበላሉ፤ እንዲሁም አክብሮት ያሳዩአቸዋል።—ምሳሌ 19:20
ቤተሰባችሁ ደስተኛ እንዲሆን አድርጉ የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦
እያንዳንዱ የቤተሰቡ አባል ለቤተሰቡ ደስታ አስተዋጽኦ ያበረከተው እንዴት ነው?