ከነሐሴ 21-27
ነህምያ 10–11
መዝሙር 37 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ለይሖዋ ሲሉ መሥዋዕት ከፍለዋል”፦ (10 ደቂቃ)
መንፈሳዊ ዕንቁዎች፦ (10 ደቂቃ)
ነህ 10:34—ሕዝቡ እንጨት ማቅረብ የነበረበት ለምንድን ነው? (w06 2/1 11 አን. 1)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ) ነህ 10:28-39 (th ጥናት 5)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (3 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ርዕሰ ጉዳይ ጀምር። ግለሰቡ በስብሰባችን ላይ እንዲገኝ ጋብዝ፤ ከዚያም በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።) (th ጥናት 1)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ርዕሰ ጉዳይ ጀምር። ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር አበርክተህ “እዚህ ጽሑፍ ላይ ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ክፍል በአጭሩ ተመልከቱ። (th ጥናት 4)
ንግግር፦ (5 ደቂቃ) w11 2/15 15-16 አን. 12-15—ጭብጥ፦ በዛሬው ጊዜ አምላክን የሚያስደስቱ መሥዋዕቶች። (th ጥናት 20)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት የትኞቹን ግቦች አውጥታችኋል?”፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ።
“በመስከረም ወር የአምላክን መንግሥት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ልዩ ዘመቻ!”፦ (5 ደቂቃ) የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግር የሚያቀርበው። አድማጮች በዘመቻው ለመካፈል ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ፤ እንዲሁም ጉባኤው ለዘመቻው ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 55 ነጥብ 1-4
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 92 እና ጸሎት