በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት የትኞቹን ግቦች አውጥታችኋል?

ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት የትኞቹን ግቦች አውጥታችኋል?

መንፈሳዊ ግብ የሚባለው ይሖዋን ይበልጥ ለማገልገልና እሱን ለማስደሰት ስንል ልንደርስበት የምንጣጣረው ማንኛውም ዕቅድ ነው። መንፈሳዊ ግቦች በእውነት ውስጥ እድገት እንድናደርግ ይረዱናል፤ እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ ስንል ጊዜያችንንም ሆነ ጉልበታችንን መሥዋዕት ብናደርግ የሚያስቆጭ አይደለም። (1ጢሞ 4:15) ግቦቻችንን አለፍ አለፍ እያልን መገምገም ያለብን ለምንድን ነው? ምክንያቱም ያለንበት ሁኔታ ይቀየራል። ቀደም ሲል ያወጣነው ግብ አሁን ካለንበት ሁኔታ አንጻር የሚደረስበት ላይሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ግቡ ላይ ደርሰን ከሆነ ሌላ ግብ ማውጣት እንችላለን።

አዲስ የአገልግሎት ዓመት ከመጀመሩ በፊት ግቦቻችንን መገምገማችን ጠቃሚ ነው። የቤተሰብ አምልኮ ስታደርጉ በዚህ ጉዳይ ላይ በመወያየት በግለሰብ ደረጃና በቤተሰብ ደረጃ ልትደርሱባቸው የምትችሉ ግቦች ለምን አታወጡም?

ከሚከተሉት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምን ግብ አውጥተሃል? ግብህ ላይ ለመድረስስ የትኞቹን እርምጃዎች ለመውሰድ አስበሃል?

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፣ የግል ጥናት፣ በስብሰባ ላይ መገኘት፣ ሐሳብ መስጠት።—w02 6/15 15 አን. 14-15

የመስክ አገልግሎት።—w23.05 27 አን. 4-5

ክርስቲያናዊ ባሕርያት።—w22.04 23 አን. 5-6

ሌላ፦