በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በመስከረም ወር የአምላክን መንግሥት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ልዩ ዘመቻ!

በመስከረም ወር የአምላክን መንግሥት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ልዩ ዘመቻ!

በመስከረም ወር፣ ለሰው ልጆች ችግሮች ብቸኛው መፍትሔ የአምላክ መንግሥት እንደሆነ ለማስተዋወቅ ልዩ ጥረት እናደርጋለን። (ማቴ 24:14) በዘመቻው መካፈል የምትችሉት እንዴት ነው? በዚያ ወር በተቻለ መጠን ለብዙ ሰው ስለ አምላክ መንግሥት የሚናገር ጥቅስ ለማንበብ ጥረት አድርጉ። የምትመሠክሩላቸው ሰዎች ፍላጎት ካሳዩ ለሕዝብ የሚሰራጨውን መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 2 2020 አበርክቱላቸው። ከዚያም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሳችሁ አነጋግሯቸው፤ እንዲሁም ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅማችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። በመስከረም ወር ረዳት አቅኚ የሚሆኑ አስፋፊዎች ለ15 ሰዓት ወይም ለ30 ሰዓት ማገልገል ይችላሉ።

የአምላክ መንግሥት የሚቃወሙትን መንግሥታት በሙሉ የሚያደቅበት ጊዜ በጣም ቀርቧል። (ዳን 2:44፤ 1ቆሮ 15:24, 25) እንግዲያው ሁላችንም ለይሖዋና ለመንግሥቱ ያለንን ታማኝነት ማሳየት የምንችልበትን ይህን ልዩ አጋጣሚ በተሟላ መንገድ እንጠቀምበት!