በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የይሖዋን ታማኝ ፍቅር ኮርጁ

የይሖዋን ታማኝ ፍቅር ኮርጁ

ይሖዋ ታማኝ ፍቅር በማሳየት ረገድ ወደር የሌለው ምሳሌ ነው። (መዝ 103:11) ታማኝ ፍቅር ጊዜያዊ የሆነ የመዋደድ ስሜት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ጥልቀት ያለውና ዘላቂ የሆነ ዝምድናን ያመለክታል። ይሖዋ ከሕዝቡ ከእስራኤላውያን ጋር በተያያዘ ይህን ባሕርይ በተለያዩ መንገዶች አንጸባርቋል። ከግብፅ ባርነት ነፃ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር አስገብቷቸዋል። (መዝ 105:42-44) ለሕዝቦቹ ተዋግቶላቸዋል፤ እንዲሁም ኃጢአት ሲሠሩ በተደጋጋሚ ይቅር ብሏቸዋል። (መዝ 107:19, 20) “ይሖዋ በታማኝ ፍቅር ያከናወናቸውን ነገሮች በትኩረት” ስንመለከት እሱን ለመኮረጅ እንነሳሳለን።—መዝ 107:43

“ይሖዋ በታማኝ ፍቅር ያከናወናቸውን ነገሮች በትኩረት” ተመልከቱ የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ታማኝ ፍቅር ማሳየት የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?

  • ታማኝ ፍቅር ማሳየት መሥዋዕት መክፈል የሚጠይቀው ለምንድን ነው?