ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ጓደኛ ስትመርጡ ለይሖዋ ታማኝ ሁኑ
አሞናውያንና ሞዓባውያን ከጥንት ጀምሮ የአምላክን ሕዝቦች ሲቃወሙ ስለኖሩ ወደ አምላክ ጉባኤ እንዳይገቡ ተከልክለው ነበር (ነህ 13:1, 2፤ it-1 95 አን. 5)
ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብ አንድ አሞናዊ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የመመገቢያ አዳራሽ እንዲያዘጋጅ ፈቅዶ ነበር (ነህ 13:4, 5፤ w13 8/15 4 አን. 5-6)
ነህምያ፣ ኤልያሺብ ከአምላክ ጠላት ጋር ያደረገውን ስምምነት በማፍረስ ለይሖዋ ታማኝ መሆኑን አሳይቷል (ነህ 13:7-9)
ይሖዋን የማይወዱ ጓደኞች ከመረጥን ለይሖዋ ታማኝ ሆነናል ሊባል ይችላል?—w96 3/15 16 አን. 6
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ይሖዋ ስለ ጓደኛ ምርጫዬ ምን ይሰማዋል?’