በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

እኛን ለማገልገል በትጋት ይሠራሉ

እኛን ለማገልገል በትጋት ይሠራሉ

የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሚስቶቻቸው ወንድሞቻቸውን በማገልገል ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ያሳያሉ። እንደ ማናችንም ሁሉ እነሱም የሚያስፈልጓቸው ነገሮች አሉ፤ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ይደክማሉ፣ ተስፋ ይቆርጣሉ ወይም ይጨነቃሉ። (ያዕ 5:17) ያም ቢሆን፣ በየሳምንቱ ትኩረት የሚያደርጉት በሚጎበኙት ጉባኤ ውስጥ ባሉ ወንድሞችና እህቶች ላይ ነው፤ እነሱን ለማበረታታትም ጥረት ያደርጋሉ። በእርግጥም የወረዳ የበላይ ተመልካቾች “እጥፍ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል።”—1ጢሞ 5:17

ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሄዶ ለእምነት አጋሮቹ ‘መንፈሳዊ ስጦታ ለማካፈል’ ባሰበ ጊዜ ከእነሱ ጋር ‘እርስ በርስ ለመበረታታት’ ጓጉቶ ነበር። (ሮም 1:11, 12) የወረዳ የበላይ ተመልካቹን እንዲሁም ያገባ ከሆነ ባለቤቱን ማበረታታት የምትችሉት እንዴት እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ?

በገጠራማ ክልል የሚያገለግል የወረዳ የበላይ ተመልካች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሚስቶቻቸው ለጉባኤው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር የሚያሳዩት በየትኞቹ መንገዶች ነው?

  • ከሚያከናውኑት ሥራ ምን ጥቅም አግኝተሃል?

  • ልናበረታታቸው የምንችለው እንዴት ነው?