በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከሐምሌ 29–ነሐሴ 4

መዝሙር 69

ከሐምሌ 29–ነሐሴ 4

መዝሙር 13 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. መዝሙር 69 ስለ ኢየሱስ ሕይወት ምን ትንቢት ይዟል?

(10 ደቂቃ)

ኢየሱስ ያለምክንያት ተጠልቷል (መዝ 69:4፤ ዮሐ 15:24, 25w11 8/15 11 አን. 17)

ኢየሱስ ለይሖዋ ቤት ቅንዓት ነበረው (መዝ 69:9፤ ዮሐ 2:13-17w10 12/15 8 አን. 7-8)

ኢየሱስ የስሜት ሥቃይ ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሐሞት የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ ተሰጥቶታል (መዝ 69:20, 21፤ ማቴ 27:34፤ ሉቃስ 22:44፤ ዮሐ 19:34g95 10/22 31 አን. 4፤ it-2 650)


ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ይሖዋ በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ መሲሐዊ ትንቢቶች እንዲካተቱ ያደረገው ለምንድን ነው?

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 69:30, 31—ይህ ጥቅስ የጸሎታችንን ይዘት ለማሻሻል የሚረዳን እንዴት ነው? (w99 1/15 18 አን. 11)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 69:1-25 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ትዕግሥት—ኢየሱስ ምን አድርጓል?

(7 ደቂቃ) ውይይት። ቪዲዮውን አጫውት ከዚያም lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 1-2 ላይ ተወያዩ።

5. ትዕግሥት—ኢየሱስን ምሰል

(8 ደቂቃ) lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3-5 እና “ተጨማሪ ጥቅሶች” ላይ የተመሠረተ ውይይት።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 134

6. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ

(5 ደቂቃ)

7. ለቤተሰብ አምልኮ ምሽት የሚጠቅሙ ምክሮች

(10 ደቂቃ) ውይይት።

ጥር 2009 የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት እና ከአገልግሎት ስብሰባ ጋር ተቀላቅሎ በሳምንቱ መሃል አንድ ስብሰባ ብቻ እንዲኖር ተደረገ። ይህም ቤተሰቦች በየሳምንቱ የራሳቸውን የቤተሰብ አምልኮ የሚያደርጉበት አንድ ምሽት እንዲያገኙ አስችሏል። ብዙዎች፣ ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡና እርስ በርስ እንዲቀራረቡ ለመርዳት ሲባል ለተደረገው ለዚህ ዝግጅት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።—ዘዳ 6:6, 7

የቤተሰብ ራሶች የቤተሰብ አምልኳቸው ስኬታማ እንዲሆን ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? አንዳንድ ምክሮችን እስቲ እንመልከት።

  • ቋሚ አድርጉት። የሚቻል ከሆነ በየሳምንቱ የቤተሰብ አምልኮ የምታደርጉበት ቋሚ ሰዓት መድቡ። ፕሮግራማችሁ ከተስተጓጎለ ሌላ አማራጭ ቀን ይኑራችሁ

  • ተዘጋጁ። የትዳር ጓደኛችሁን ማማከር እንዲሁም አልፎ አልፎ የልጆቻችሁን አስተያየት መጠየቅ ትችላላችሁ። በተለይ ቤተሰቡ በየሳምንቱ ተመሳሳይ ነገሮችን ማድረግ የሚያስደስተው ከሆነ ለዝግጅት ረጅም ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግ ይሆናል

  • ፕሮግራሙ የቤተሰቡን ሁኔታ ያማከለ እንዲሆን አድርጉ። ልጆች እያደጉ ሲሄዱ የሚያስፈልጋቸው ነገርና ችሎታቸው ይቀየራል። ፕሮግራማችሁ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በመንፈሳዊ እንዲያድግ የሚረዳ ሊሆን ይገባል

  • ፍቅርና ዘና ያለ መንፈስ እንዲሰፍን አድርጉ። አንዳንድ ጊዜ የአየር ሁኔታው አመቺ ከሆነ ደጅ ማጥናት ትችሉ ይሆናል። እንደ አስፈላጊነቱ በየመሃል እረፍት ማድረግ ትችላላችሁ። በቤተሰቡ ውስጥ ላጋጠሙ ችግሮች ትኩረት መስጠት ቢኖርባችሁም የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራሙን ለመውቀስ ወይም ተግሣጽ ለመስጠት አትጠቀሙበት

  • የተለያዩ ነገሮችን አድርጉ። ለምሳሌ የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ከቀጣዩ ስብሰባ ላይ የተወሰነውን ክፍል መዘጋጀትን፣ jw.org ላይ የሚገኝን ቪዲዮ ተመልክቶ መወያየትን እንዲሁም ለአገልግሎት ልምምድ ማድረግን ሊያካትት ይችላል። የቤተሰብ አምልኮ ምሽት ዋነኛ ክፍል ውይይት መሆን ቢኖርበትም የቤተሰቡ አባላት የግል ጥናት እንዲያደርጉ ጊዜ መመደብ ይቻላል

በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • እነዚህን ምክሮች በቤተሰብ አምልኳችሁ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የሞከራችሁት እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 114 እና ጸሎት