በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከነሐሴ 5-11

መዝሙር 70–72

ከነሐሴ 5-11

መዝሙር 59 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ለቀጣዩ ትውልድ” ስለ አምላክ ኃይል ተናገሩ

(10 ደቂቃ)

ዳዊት በወጣትነቱ የይሖዋን ጥበቃ አግኝቷል (መዝ 71:5w99 9/1 18 አን. 17)

ዳዊት በስተ እርጅናው የይሖዋን ድጋፍ አጣጥሟል (መዝ 71:9g04 10/8 23 አን. 3)

ዳዊት ተሞክሮውን በመናገር ወጣቶችን አበረታቷል (መዝ 71:17, 18w14 1/15 23 አን. 4-5)

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በቤተሰብ አምልኳችን ላይ በጉባኤያችን ውስጥ ካሉት ለረጅም ጊዜ ይሖዋን ያገለገሉ ክርስቲያኖች መካከል ለማን ቃለ መጠይቅ ማድረግ እችላለሁ?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 72:8—ይሖዋ በዘፍጥረት 15:18 ላይ ለአብርሃም የገባው ቃል በንጉሥ ሰለሞን የግዛት ዘመን ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (it-1 768)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 71:1-24 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መከራከር ሲጀምር ውይይቱን አዎንታዊ በሆነ መንገድ አቁም። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ከአንድ ዘመድህ ጋር ቀደም ሲል የጀመርከውን ውይይት ቀጥል፤ ግለሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር እያመነታ ነው። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 4)

6. እምነታችንን ማብራራት

(5 ደቂቃ) ንግግር። ijwfq 49—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ከሚያምኑባቸው ነገሮች አንዳንዶቹን የቀየሩት ለምንድን ነው? (th ጥናት 17)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 76

7. ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች

(15 ደቂቃ) ውይይት።

የቤተሰብ አምልኮ፣ ልጆች ስለ “ይሖዋ ተግሣጽና ምክር” የሚማሩበት ግሩም አጋጣሚ ይፈጥራል። (ኤፌ 6:4) መማር ሥራ ይጠይቃል፤ ሆኖም በተለይ ልጆች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ጉጉት እያዳበሩ ሲሄዱ መማር አስደሳች ሊሆንላቸው ይችላል። (ዮሐ 6:27፤ 1ጴጥ 2:2) ወላጆች የቤተሰብ አምልኳቸውን ትምህርት ሰጪና አስደሳች እንዲያደርጉ ለመርዳት የተዘጋጀውን “ ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች” የሚለውን ሣጥን ከልስ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ከእነዚህ ሐሳቦች መካከል የትኛውን መሞከር ትፈልጋላችሁ?

  • ጠቃሚ ሆኖ ያገኛችሁት ሌላ ነገር አለ?

የቤተሰብ አምልኳችሁን ማሻሻላችሁን ቀጥሉ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ልጆች ከሌሉ አንድ ባል የቤተሰብ አምልኮውን ለሚስቱ አስደሳች ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 123 እና ጸሎት