በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለአንድ ዓመት መሞከር ትችላለህ?

ለአንድ ዓመት መሞከር ትችላለህ?

ምኑን? የዘወትር አቅኚነትን! የሚያስገኝልህን የተትረፈረፈ በረከት ተመልከት!—ምሳሌ 10:22

አቅኚ ከሆንክ . . .

  • ለወንጌላዊ የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን ታዳብራለህ እንዲሁም በአገልግሎት ይበልጥ ትደሰታለህ

  • ከይሖዋ ጋር ያለህ ዝምድና ይጠናከራል። ስለ ይሖዋ ለሌሎች በተናገርክ መጠን አስደናቂ የሆኑ ባሕርያቱ ይበልጥ እውን ይሆኑልሃል

  • ከራስ ፍላጎት ይልቅ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማስቀደም የሚያስገኘውን እርካታና ሌሎችን ለመርዳት ራስን ማቅረብ የሚያስገኘውን ደስታ ታጣጥማለህ። —ማቴ 6:33፤ ሥራ 20:35

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን በሚጎበኝበት ወቅት ከአቅኚዎች ጋር በሚያደርገው ስብሰባ፣ ከወረዳ ስብሰባ ጋር ተያይዞ በሚደረገው ልዩ ስብሰባ እንዲሁም በአቅኚነት ትምህርት ቤት የመካፈል መብት ታገኛለህ

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመርና ጥናት የመምራት አጋጣሚህ ሰፊ ይሆናል

  • አብረውህ ከሚያገለግሉት ጋር ይበልጥ ሰፋ ያለ ጊዜ የማሳለፍና እርስ በርስ የመበረታታት አጋጣሚ ታገኛለህ።—ሮም 1:11, 12