በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ

ጥያቄ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ያጻፈው አምላክ ከሆነ መጽሐፉን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ጥረት አይሳካም ቢባል አይስማሙም?

ጥቅስ፦ ኢሳ 40:8

አበርክት፦ ይህ ተከታታይ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥፋት የተደረጉት ጥረቶች የከሸፉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

መጠበቂያ ግንብ (የጀርባ ሽፋን)

ጥያቄ፦ ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ? [በገጽ 16 ላይ የሚገኘውን የመጀመሪያውን ጥያቄ አንብብ።] አንዳንዶች፣ ሃይማኖት ሰዎች የፈጠሩት ነገር እንደሆነ ይሰማቸዋል? ሌሎች ደግሞ ሃይማኖት አምላክ ወደ እሱ እንድንቀርብ የሚጠቀምበት መንገድ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይላሉ?

ጥቅስ፦ ያዕ 1:27 ግርጌ

አበርክት፦ ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ተጨማሪ ሐሳብ ይዟል። በሌላ ጊዜ መጥቼ በዚህ ጉዳይ ላይ ብንወያይ ደስ ይለኛል።

ከአምላክ የተላከ ምሥራች!

ጥያቄ፦ ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ትንቢቶች ሲያነቡ ልክ አሁን እንደተጻፉ ዜናዎች ሆነው ይሰሟቸዋል። እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ነገሮች መካከል እርስዎ ሲፈጸም ያዩት ወይም የሰሙት የትኛውን ነው?

ጥቅስ፦ 2ጢሞ 3:1-5

አበርክት፦ ይህ ብሮሹር እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸው አምላክን ለሚወዱ ሰዎች ምሥራች ነው የሚባለው ለምን እንደሆነ ያብራራል። [ትምህርት 1 ጥያቄ 2 ላይ የሚገኙትን አንዳንድ ነጥቦች ጥቀስ።]

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።