በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 60-68

ጸሎት ሰሚ የሆነውን ይሖዋን አወድሱ

ጸሎት ሰሚ የሆነውን ይሖዋን አወድሱ

ለይሖዋ የገባችሁትን ቃል መፈጸም እንድትችሉ ጸልዩ

61:1, 8

  • የገባነውን ቃል አስመልክቶ መጸለያችን ቃላችንን ለመጠበቅ ያደረግነውን ውሳኔ ያጠናክርልናል

  • ከምንም ነገር በላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ራሳችንን ለይሖዋ ስንወስን የገባነው ቃል ነው

ሐና

በጸሎት አማካኝነት የልባችሁን አውጥታችሁ በመናገር በይሖዋ እንደምትተማመኑ አሳዩ

62:8

  • ትርጉም ያለው ጸሎት፣ የልብን አውጥቶ መጸለይን ይጨምራል

  • ስንጸልይ የምንፈልገውን ለይተን የምንጠቅስ ከሆነ ይሖዋ የሚሰጠንን መልስ ይበልጥ ማስተዋል እንችላለን

ኢየሱስ

ይሖዋ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች የሚያቀርቡትን ጸሎት ሁሉ ይሰማል

65:1, 2

  • ይሖዋ “ሁሉም ዓይነት ሰዎች” እሱን ለማወቅና ፈቃዱን ለማድረግ ከልብ ጥረት እስካደረጉ ድረስ የሚያቀርቡትን ጸሎት ይሰማል

  • በማንኛው ጊዜ ወደ ይሖዋ መጸለይ እንችላለን

ቆርኔሌዎስ

በጸሎትህ ውስጥ ልታካትታቸው የምትፈልጋቸውን ጉዳዮች ጻፍ