በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሉቃስ 6-7

በልግስና ስፈሩ

በልግስና ስፈሩ

6:38

ለጋስ የሆነ ሰው ሌሎችን ለመርዳትና ለማበረታታት ጊዜውን፣ ጉልበቱንና ጥሪቱን በደስታ ይሰጣል።

  • “ስጡ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ግስ ቀጣይነት ያለውን ድርጊት ያመለክታል

  • ሰጪዎች ከሆን ሌሎችም “ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው” በእቅፋችን ይሰጡናል። በጥንት ጊዜ የነበሩ ነጋዴዎች አንድ ገበያተኛ የገዛቸውን ነገሮች በልብሱ እጥፋት ውስጥ የመሙላት ልማድ ነበራቸው፤ ‘ሰፍሮ በእቅፍ መስጠት’ የሚለው አገላለጽ ይህን ልማድ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል