በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የማስተዋል ችሎታችሁን አሠልጥኑ

የማስተዋል ችሎታችሁን አሠልጥኑ

አንድ ስፖርተኛ ብቃቱን ይዞ ለመቀጠል ሁልጊዜ ልምምድ በማድረግ ጡንቻዎቹን ማሠራት አለበት። በተመሳሳይ እኛም፣ የማስተዋል ችሎታችንን ለማሠልጠንና ይህን ችሎታችንን ይዘን ለመቀጠል የማያቋርጥ ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል። (ዕብ 5:14) እርግጥ ነው፣ ብዙ ጊዜ የሚቀናን የሌሎችን ውሳኔ አይተን በዚያ መሠረት መወሰን ሊሆን ይችላል፤ ይሁንና የማሰብ ችሎታችንን ማሠራትና የራሳችንን ውሳኔ ማድረግ ይኖርብናል። ለምን? ምክንያቱም እያንዳንዳችን ለምናደርገው ውሳኔ ለአምላክ መልስ እንሰጣለን።—ሮም 14:12

በእውነት ቤት ረጅም ዓመት ስለቆየን ብቻ ጥሩ ውሳኔ እንደምናደርግ ሊሰማን አይገባም። ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ ከይሖዋ፣ ከቃሉና ከድርጅቱ በምናገኘው እርዳታ ሙሉ በሙሉ መጠቀም ይኖርብናል።—ኢያሱ 1:7, 8፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ ማቴ 24:45

“ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ኤማ፣ ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቅ ምን ሁኔታ አጋጥሟት ነበር?

  • ለሕሊና ከተተዉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የራሳችንን አመለካከት በሌሎች ላይ መጫን የሌለብን ለምንድን ነው?

  • አንድ ባልና ሚስት ለኤማ ምን ጥሩ ምክር ሰጥተዋታል?

  • ኤማ፣ ላለችበት ሁኔታ የሚሠራ ጠቃሚ መረጃ ያገኘችው ከየት ነው?