ክርስቲያናዊ ሕይወት
ሁሌም ይሖዋን አስቡ
ሥራ ማግኘት አስቸጋሪ በሚሆንበት ወቅት የአምላክን መንግሥትና ጽድቅ ማስቀደም ከባድ ሊሆንብን ይችላል። ለይሖዋ የምናቀርበውን አገልግሎት የሚነካ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንድንጥስ የሚያደርግ ሥራ ለመቀበል እንፈተን ይሆናል። ሆኖም ይሖዋ ‘በሙሉ ልባቸው ወደ እሱ ያዘነበሉ ሰዎችን’ ለመርዳት ኃይሉን እንደሚጠቀም እርግጠኞች መሆን እንችላለን። (2ዜና 16:9) አፍቃሪው አባታችን እኛን ከመርዳትና የሚያስፈልገንን ነገር ከማሟላት ሊያግደው የሚችል ምንም ነገር የለም። (ሮም 8:32) በመሆኑም ከሥራ ጋር የተያያዘ ውሳኔ ስናደርግ፣ በይሖዋ መታመንና በሕይወታችን ውስጥ ምንጊዜም ለእሱ አገልግሎት ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል።—መዝ 16:8
ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ጄሰን ጉቦ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነው ለምንድን ነው?
-
ቆላስይስ 3:23ን ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
-
ጄሰን የተወው ምሳሌ በቶማስ ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል?
-
ማቴዎስ 6:22ን ልንሠራበት የምንችለው እንዴት ነው?