በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ትዳር—የዕድሜ ልክ ጥምረት

ትዳር—የዕድሜ ልክ ጥምረት

ስኬታማ ትዳር ይሖዋን ያስከብራል፤ ለባልና ሚስቱም ደስታ ያስገኛል። (ማር 10:9) ክርስቲያኖች ዘላቂና ደስተኛ ትዳር መመሥረት ከፈለጉ የትዳር ጓደኛቸውን ሲመርጡ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በጥብቅ መከተል ይኖርባቸዋል።

“አፍላ የጉርምስና ዕድሜ” ሳያልፍ መጠናናት አለመጀመር ጥበብ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ ዕድሜ ላይ የፆታ ስሜት ስለሚያይል ጥሩ ውሳኔ የማድረግ ችሎታን ሊያዛባ ይችላል። (1ቆሮ 7:36) በነጠላነት የምትቆዩበትን ጊዜ በጥበብ ተጠቀሙበት፤ ከአምላክ ጋር ያላችሁን ዝምድና ለማጠናከርና ክርስቲያናዊ ባሕርያትን ለማዳበር ጥረት አድርጉ። ይህም በኋላ ላይ ትዳር ሲመጣ ጥሩ አጋር እንድትሆኑ ያስችላችኋል።

አንድን ሰው ለማግባት ከመወሰናችሁ በፊት ጊዜ ወስዳችሁ የግለሰቡን “የተሰወረ የልብ ሰው” ለማወቅ ጥረት አድርጉ። (1ጴጥ 3:4) ጥርጣሬ የሚፈጥርባችሁ ከበድ ያለ ነገር ካስተዋላችሁ ልታገቡት ላሰባችሁት ሰው አንሱለት። እንደ ማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሁሉ ትዳር ላይም ቅድሚያ የሚሰጠው ‘ምን አገኛለሁ’ የሚለው ሳይሆን ‘ምን እሰጣለሁ’ የሚለው እንደሆነ አትርሱ። (ፊልጵ 2:3, 4) ከትዳር በፊት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ ለደስተኛ ትዳር መሠረት መጣል ትችላላችሁ።

ለጋብቻ መዘጋጀት—ክፍል 3፦ ‘ወጪያችሁን አስሉ’ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • እህታችንና ሼን መጀመሪያ ላይ የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስላል?

  • ጊዜ እያለፈ ሲሄድ እህት ምን አስተዋለች?

  • ወላጆቿ የረዷት እንዴት ነው? ምን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔስ አድርጋለች?