ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ባለን መርካትና ልካችንን ማወቅ—ለምን?
የአምላክ ነቢይ የኢዮርብዓምን ውድ ስጦታዎች ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም (1ነገ 13:7-10፤ w08 8/15 8 አን. 4)
በኋላ ላይ የአምላክ ነቢይ ይሖዋ የሰጠውን ግልጽ ትእዛዝ ጣሰ (1ነገ 13:14-19፤ w08 8/15 11 አን. 15)
ነቢዩ አለመታዘዙ መዘዝ አስከትሎበታል (1ነገ 13:20-22፤ w08 8/15 9 አን. 10)
ባለን የምንረካና ውሳኔ ስናደርግ የይሖዋን መመሪያ የምንጠይቅ ከሆነ ካልጠበቅናቸው ብዙ ችግሮች እንድናለን።—1ጢሞ 6:8-10
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ለኑሮ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ነገሮች ከተሟሉልኝ በዚያ ረክቼ እንደምኖር የማሳየው እንዴት ነው? ውሳኔ ሳደርግ ልኬን እንደማውቅ የማሳየው እንዴት ነው?’—ምሳሌ 3:5፤ 11:2