ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
አሳ በድፍረት እርምጃ ወስዷል—አንተስ?
አሳ ለንጹሕ አምልኮ ሲል በቅንዓት እርምጃ ወስዷል (1ነገ 15:11, 12፤ w12 8/15 8 አን. 4)
አሳ ከቤተሰቡ ይልቅ አምልኮውን በማስቀደም ድፍረት አሳይቷል (1ነገ 15:13፤ w17.03 19 አን. 7)
ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው፣ የአሳ መልካም ባሕርያት ስህተቶቹን ሸፍነውለታል (1ነገ 15:14, 23፤ it-1 184-185)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ለንጹሕ አምልኮ ቅንዓት እንዳለኝ አሳያለሁ? የቤተሰቤ አባል ቢሆን እንኳ ለይሖዋ ጀርባውን ከሚሰጥ ሰው ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጣለሁ?’—2ዮሐ 9, 10