ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውን ያድናል
ሁሉም ሰው አልፎ አልፎ ያዝናል። የሐዘን ስሜት የመንፈሳዊ ድክመት ምልክት አይደለም። ይሖዋም እንኳ ሳይቀር ሐዘን የተሰማው ጊዜ እንዳለ ገልጿል። (ዘፍ 6:5, 6) ይሁንና በተደጋጋሚ ወይም ሁልጊዜ በሐዘን ስሜት ብንዋጥስ?
ይሖዋ እንዲረዳችሁ ጸልዩ። ይሖዋ አእምሯዊና ስሜታዊ ጤንነታችን በጣም ያሳስበዋል። ስንደሰትና ስናዝን ያስተውላል። በአስተሳሰባችንና በስሜታችን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩትን ነገሮች ይረዳል። (መዝ 7:9ለ) ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ይሖዋ በጣም ያስብልናል፤ እንዲሁም ሐዘንን አልፎ ተርፎም የመንፈስ ጭንቀትን ለመቋቋም ይረዳናል።—መዝ 34:18
የአእምሮ ጤንነታችሁን ተንከባከቡ። አሉታዊ ስሜቶች ደስታችንንም ሆነ አምልኳችንን ሊነኩ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ ልባችንን ማለትም መላውን ውስጣዊ ማንነታችንን መጠበቅ ይኖርብናል።—ምሳሌ 4:23
ወንድሞቻችን ሰላማቸውን ጠብቀው እየኖሩ ያሉት እንዴት ነው?—የመንፈስ ጭንቀት ቢያጋጥማቸውም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ኒኪ ከመንፈስ ጭንቀት ጋር የምታደርገውን ትግል ለማሸነፍ ምን ተግባራዊ እርምጃዎችን ወስዳለች?
-
ኒኪ የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት የተሰማት ለምንድን ነው?—ማቴ 9:12
-
ኒኪ በይሖዋ እርዳታ እንደምትታመን ያሳየችው በየትኞቹ መንገዶች ነው?