በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመስከረም 2-8

መዝሙር 79–81

ከመስከረም 2-8

መዝሙር 29 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ለይሖዋ ታላቅ ስም ያላችሁን ፍቅር አሳዩ

(10 ደቂቃ)

ይሖዋን ከሚያሰድቡ ድርጊቶች ራቁ (መዝ 79:9w17.02 9 አን. 5)

የይሖዋን ስም ጥሩ (መዝ 80:18ijwbv 3 አን. 4-5)

ይሖዋ ታዛዥ በመሆን ለስሙ ያላቸውን ፍቅር የሚያሳዩ ሰዎችን አትረፍርፎ ይባርካል (መዝ 81:13, 16)

ምግባራችን የይሖዋን ስም እንዲያስከብር ከፈለግን የእሱ ምሥክሮች መሆናችንን መናገር አለብን

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 80:1—የዮሴፍ ስም አንዳንድ ጊዜ ሁሉንም የእስራኤል ነገዶች ለማመልከት የተሠራበት ለምንድን ነው? (it-2 111)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(1 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 4)

5. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)

6. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)

7. ተመላልሶ መጠየቅ

(5 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ቀደም ሲል መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፈቃደኛ ያልነበረን ሰው ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 10

8. “ስሜን ይቀድሳሉ”

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ሰይጣን የይሖዋን ስም ማጥፋት የጀመረው በኤደን ገነት ነው። ከዚያ ጊዜ አንስቶ፣ ማሰብ በሚችሉ ፍጥረታት ሁሉ ፊት የተደቀነው አንገብጋቢ ጉዳይ የይሖዋ ስም ከነቀፋ ነፃ መሆን ነው።

ሰይጣን ስለ ይሖዋ ካስፋፋቸው መርዘኛ ውሸቶች መካከል አንዳንዶቹን እስቲ እንመልከት። ይሖዋን ጨካኝና ፍቅር የሌለው ገዢ ነው በማለት ወንጅሎታል። (ዘፍ 3:1-6፤ ኢዮብ 4:18, 19) የይሖዋ አገልጋዮች ለእሱ እውነተኛ ፍቅር እንደሌላቸው ተናግሯል። (ኢዮብ 2:4, 5) ይባስ ብሎም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማታለል በዙሪያችን ያለውን ውብ ዓለም የፈጠረው ይሖዋ እንዳልሆነ አሳምኗቸዋል።—ሮም 1:20, 21

እነዚህን ውሸቶች ስትሰማ ምን ይሰማሃል? ለይሖዋ ጥብቅና ለመቆም እንደምትነሳሳ ምንም ጥያቄ የለውም! ይሖዋ ሕዝቦቹ ስሙን ማስቀደስ እንደሚፈልጉ ያውቃል። (ከኢሳይያስ 29:23 ጋር አወዳድር።) አንተስ የበኩልህን አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችለው እንዴት ነው?

  • ሌሎች ይሖዋን እንዲያውቁትና እንዲወዱት እርዳቸው። (ዮሐ 17:25, 26) እሱ በእርግጥ መኖሩን የሚያሳየውን ማስረጃ ለማቅረብ እንዲሁም ስለ ግሩም ባሕርያቱ ሌሎችን ለማስተማር ዝግጁ ሁን።—ኢሳ 63:7

  • ይሖዋን በሙሉ ልብህ ውደድ። (ማቴ 22:37, 38) የይሖዋን ትእዛዛት አክብር፤ ይህን የምታደርገው ትእዛዛቱ ስለሚጠቅሙህ ብቻ ሳይሆን እሱን ማስደሰት ስለምትፈልግ መሆን አለበት።—ምሳሌ 27:11

ፍቅር ለዘላለም ይኖራል—በትምህርት ቤት መጥፎ ተጽዕኖ ቢኖርም የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ኤሪየል እና ዲዬጎ ለይሖዋ ስም ጥብቅና የቆሙት እንዴት ነው?

  • ለይሖዋ ስም ጥብቅና እንዲቆሙ ያነሳሳቸው ምንድን ነው?

  • የእነሱን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 90 እና ጸሎት