በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥቅምት 7-13

መዝሙር 92–95

ከጥቅምት 7-13

መዝሙር 84 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ይሖዋን ማገልገል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት ጎዳና ነው!

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ አምልኳችን ይገባዋል (መዝ 92:1, 4w18.04 26 አን. 5)

ለሕዝቦቹ ወደር የሌለው ጥልቅ ማስተዋል ይሰጣቸዋል (መዝ 92:5w18.11 20 አን. 8)

አገልጋዮቹ ባረጁ ጊዜም እንኳ ከፍ አድርጎ ይመለከታቸዋል (መዝ 92:12-15w20.01 19 አን. 18)

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ራሴን ለይሖዋ ወስኜ እንዳልጠመቅ ያገደኝ ምንድን ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 92:5—እነዚህ ቃላት የይሖዋን ጥበብ ጥሩ አድርገው የሚገልጹት እንዴት ነው? (cl 176 አን. 18)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 94:1-23 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የምታከናውነውን መጽሐፍ ቅዱስን የማስተማር ሥራ አስመልክቶ ለግለሰቡ ለመናገር የሚያስችል አጋጣሚ ፍጠር። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ቀደም ሲል መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፈቃደኛ ያልነበረን ሰው ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) እድገት ከማያደርግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር የሚደረግ ውይይት። (lmd ምዕራፍ 12 ነጥብ 5)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 5

7. ወጣቶች በጭንቀት ሲዋጡ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋን የሚያገለግሉ ሰዎችም ከጭንቀት ነፃ የሆነ ሕይወት አይመሩም። ለምሳሌ ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ጭንቀት አጋጥሞታል። በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ወንድሞቻችንም ጭንቀት ያጋጥማቸዋል። (መዝ 13:2፤ 139:23) የሚያሳዝነው፣ ወጣቶችም እንኳ በጭንቀት ሊዋጡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ፣ የሚሰማቸው ጭንቀት ትምህርት ቤት እንደመሄድ ወይም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንደመገኘት ያሉ የተለመዱ እንቅስቃሴዎችም እንኳ በጣም እንዲከብዷቸው ሊያደርግ ይችላል። ምናልባትም ድንገተኛ የሆነ የመሸበር ስሜት ሊያድርባቸው፣ ይባስ ብሎም ራሳቸውን የማጥፋት ሐሳብ ሊመጣባቸው ይችላል።

ወጣቶች፣ ጭንቀት የሚያስቸግራችሁ ከሆነ ወላጆቻችሁን ወይም አንድን የጎለመሰ ሰው እርዳታ ጠይቁ። ይሖዋንም እንዲደግፋችሁ ጠይቁት። (ፊልጵ 4:6) እሱ ይረዳችኋል። (መዝ 94:17-19፤ ኢሳ 41:10) የስቲንግን ምሳሌ እንመልከት።

ይሖዋ ስለ እኔ ያስባል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

• ስቲንግን የረዳው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ነው? ለምንስ?

• ይሖዋ የተንከባከበው እንዴት ነው?

ወላጆች፣ ልጆቻችሁን በትዕግሥት በማዳመጥ፣ ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር በመግለጽ እንዲሁም ይሖዋ እንደሚወዳቸው እንዲተማመኑ በመርዳት ልጆቻችሁ ጭንቀትን እንዲቋቋሙ መርዳት ትችላላችሁ። (ቲቶ 2:4፤ ያዕ 1:19) ልጆቻችሁን ለመደገፍ የሚያስችል ብርታትና ጥንካሬ እንዲሰጣችሁ ይሖዋን ጠይቁት።

በጉባኤያችን ውስጥ ማን ከከባድ ጭንቀት ጋር እየታገለ እንዳለ አናውቅ ወይም ስሜቱን መረዳት አንችል ይሆናል። ያም ቢሆን፣ በጉባኤው ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ እንደምንወዳቸውና ከፍ አድርገን እንደምንመለከታቸው እንዲሰማቸው በማድረግ የበኩላችንን እርዳታ ማበርከት እንችላለን።—ምሳሌ 12:25፤ ዕብ 10:24

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 81 እና ጸሎት