በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 135-141

ግሩምና ድንቅ ሆነን ተፈጥረናል

ግሩምና ድንቅ ሆነን ተፈጥረናል

ዳዊት በይሖዋ ፍጥረታት ላይ በተንጸባረቁት የአምላክ ግሩም ባሕርያት ላይ ያሰላስል ነበር። ዳዊት በልበ ሙሉነት ሕይወቱን ይሖዋን ለማገልገል ተጠቅሞበታል።

ዳዊት በይሖዋ ፍጥረት ላይ በጥልቀት ማሰላሰሉ ይሖዋን እንዲያወድስ ገፋፍቶታል፦

139:14

  • “በሚያስደምም ሁኔታ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ስለተፈጠርኩ አወድስሃለሁ”

139:15

  • “በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣ በማህፀን ውስጥ እያደግኩ በነበረበት ወቅት፣ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ነበር”

139:16

  • “ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ፤ የአካሌ ክፍሎች በሙሉ በመጽሐፍህ ተጻፉ”