በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ማድረግ የሌሉብን ነገሮች

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ማድረግ የሌሉብን ነገሮች

ብዙ ማውራት፦ ሁሉንም ነገር አንተ ማብራራት እንዳለብህ ሊሰማህ አይገባም። ኢየሱስ ጥያቄዎችን በመጠቀም አድማጮቹ ራሳቸው አስበው ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ረድቷቸዋል። (ማቴ 17:24-27) ጥያቄዎች ውይይቱ አስደሳች እንዲሆን እንዲሁም ተማሪው ትምህርቱ ገብቶትና አምኖበት እንደሆነ ለማወቅ ያስችላሉ። (be 253 አን. 3-4) ጥያቄ ከጠየቅክ በኋላ ተማሪው መልስ እስኪሰጥ ድረስ በትዕግሥት ጠብቀው። የሰጠው መልስ የተሳሳተ ከሆነ ትክክለኛውን መልስ ከመናገር ይልቅ ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠቀም እሱ ራሱ ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ እርዳው። (be 238 አን. 1-2) አዳዲስ ሐሳቦችን መናገር ያለብህ ተማሪው ሐሳቡን እንዲረዳው በሚያስችለው ፍጥነት መሆን አለበት።—be 230 አን. 4

ትምህርቱን ማወሳሰብ፦ ስለምትወያዩበት ርዕሰ ጉዳይ የምታውቀውን ነገር ሁሉ ከመናገር ተቆጠብ። (ዮሐ 16:12) በአንቀጹ ዋና ነጥብ ላይ ትኩረት አድርግ። (be 226 አን. 4-5) አንዳንድ ዝርዝር ነጥቦች ትኩረት የሚስቡ ቢሆኑም እንኳ ዋናው ነጥብ እንዲድበሰበስ ሊያደርጉ ይችላሉ። (be 235 አን. 3) ተማሪው ዋናው ነጥብ ግልጽ ከሆነለት ወደ ቀጣዩ አንቀጽ እለፍ።

ምዕራፉን ብቻ ለመሸፈን መጣር፦ ዋናው ዓላማችን ጽሑፉ ላይ ያለውን ሐሳብ መሸፈን ሳይሆን የተማሪውን ልብ መንካት ነው። (ሉቃስ 24:32) በትምህርቱ ውስጥ ያሉትን ቁልፍ ጥቅሶች በሚገባ በማብራራት የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል ተጠቀምበት። (2ቆሮ 10:4፤ ዕብ 4:12be 144 አን. 1-3) ቀላል ምሳሌዎችን ተጠቀም። (be 245 አን. 2-4) ተማሪው ያሉበትን ችግሮችና የሚያምንባቸውን ነገሮች ግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርቱን ለተማሪው በሚስማማ መንገድ ለማቅረብ ሞክር። እንደሚከተለው ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቅ፦ “አሁን ስለተወያየንበት ጉዳይ ምን ይሰማሃል?” “ይህ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?” “ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ምን ጥቅም የሚያስገኝ ይመስልሃል?”—be 238 አን. 3-5፤ 259 አን. 1