በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ማበረታታት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ማበረታታት

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ስብሰባዎች፣ አዘውትረን ‘ለይሖዋ ለመዘመርና’ እሱን ‘ለማወደስ’ የሚያስችል አጋጣሚ ይሰጡናል። (መዝ 149:1) የአምላክን ፈቃድ መፈጸም የምንችለው እንዴት እንደሆነ በስብሰባዎች ላይ እንማራለን። (መዝ 143:10) አብዛኛውን ጊዜ፣ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በስብሰባዎች ላይ መገኘት ከጀመሩ በኋላ ፈጣን እድገት ያደርጋሉ።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • በተቻለ ፍጥነት ሰዎችን በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ጋብዝ። ይህን ለማድረግ ግለሰቡ ቋሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እስኪጀምር ድረስ መጠበቅ አያስፈልግህም።—ራእይ 22:17

  • ፍላጎት ላሳየው ግለሰብ ስብሰባዎቻችን ላይ ምን እንደሚደረግና በቀጣዩ ስብሰባ ላይ የትኞቹ ክፍሎች እንደሚቀርቡ ንገረው። በዚህ ረገድ የሚከተሉት ዝግጅቶች ሊረዱህ ይችላሉ፦ የጉባኤ ስብሰባ መጋበዣ ወረቀት፣ በመንግሥት አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የተባለው ቪዲዮ እንዲሁም የይሖዋ ፈቃድ የተባለው ብሮሹር ትምህርት 5 እና 7

  • አስፈላጊውን እርዳታ ስጥ። ፍላጎት ያሳየው ግለሰብ ወደ ስብሰባ በመኪና የሚወስደው ሰው ያስፈልገው ይሆን? ወይም ለስብሰባው ተስማሚ የሆነ ልብስ እንዲመርጥ እርዳታ ያስፈልገዋል? በስብሰባው ላይ አጠገቡ ተቀምጠህ የሚጠኑትን ጽሑፎች አሳየው። በጉባኤው ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር አስተዋውቀው