በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በሩን ትንሽ ልጅ ሲከፍት

በሩን ትንሽ ልጅ ሲከፍት

ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል በሩን የከፈተው ትንሽ ልጅ ከሆነ ወላጆቹን እንዲጠራልን መጠየቅ ይኖርብናል። እንዲህ ማድረጋችን ወላጆቹ ላላቸው ሥልጣን አክብሮት እንዳለን ያሳያል። (ምሳሌ 6:20) ልጁ ወደቤት እንድንገባ ቢጠይቀን እንኳ ፈቃደኛ መሆን የለብንም። ወላጆቹን ቤት ማግኘት ካልቻልን ሌላ ጊዜ መመለስ ይኖርብናል።

ልጁ ከፍ ያለ፣ ምናልባትም በአሥራዎቹ ዕድሜ መጨረሻ አካባቢ ላይ የሚገኝ ቢሆን እንኳ መጀመሪያ ወላጆቹን እንዲጠራልን መጠየቅ ይኖርብናል። ወላጆቹን ማግኘት ካልቻልን ደግሞ የፈለገውን ጽሑፍ እንዲያነብ ወላጆቹ ይፈቅዱለት እንደሆነ ልንጠይቀው እንችላለን። የሚፈቅዱለት ከሆነ ጽሑፍ ልንሰጠው፣ ምናልባትም jw.org የተባለውን ድረ ገጻችንን እንዲጎበኝ ልንጋብዘው እንችላለን።

ፍላጎት ላሳየ ታዳጊ ወጣት ተመላልሶ መጠይቅ ስናደርግም ወላጆቹን ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረባችን ተገቢ ነው። ይህን ማድረጋችን የመጣንበትን ምክንያት እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተሰቦች የሚሰጠውን አስተማማኝ ምክር ለወላጆቹ ለመግለጽ ያስችለናል። (መዝ 119:86, 138) በዚህ መንገድ ለወላጆቹ አክብሮትና አሳቢነት ማሳየታችን ጥሩ ምሥክርነት የሚሰጥ ሲሆን ለቤተሰቡ ምሥራቹን የመስበክ አጋጣሚ ሊከፍትልን ይችላል።—1ጴጥ 2:12