በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 119

’በይሖዋ ሕግ ተመላለሱ’

’በይሖዋ ሕግ ተመላለሱ’

በይሖዋ ሕግ መመላለስ ሲባል ለመለኮታዊ አመራር ራሳችንን በፈቃደኝነት ማስገዛት ማለት ነው። እንደ መዝሙራዊው ሁሉ የይሖዋን ሕግ በመከተልና በእሱ በመታመን ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን።

እውነተኛ ደስታ ማግኘታችን የተመካው በአምላክ ሕግ በመመራታችን ላይ ነው

119: 1-8

ኢያሱ ይሖዋ በሚሰጣቸው መመሪያዎች ላይ ሙሉ እምነት እንዳለው አሳይቷል። ደስተኛና ስኬታማ መሆን የሚችለው በሙሉ ልቡ በይሖዋ ከታመነ ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር

የአምላክ ቃል በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን መከራዎች የምንቋቋምበት ድፍረት ይሰጠናል

119:33-40

ኤርምያስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙትም ድፍረት እንዳለውና በይሖዋ እንደሚታመን አሳይቷል። ቀላል ሕይወት ይመራ የነበረ ከመሆኑም ሌላ የተሰጠውን ኃላፊነት በጽናት ተወጥቷል

ስለ አምላክ ቃል ትክክለኛ እውቀት ማግኘታችን በልበ ሙሉነት እንድንመሠክር ያደርገናል

119:41-48

ጳውሎስ የአምላክን መልእክት ያለምንም ፍርሃት ለሁሉም ሰው ይሰብክ ነበር። ለአገረ ገዢው ለፊሊክስ በሰበከበት ወቅት ይሖዋ እንደሚረዳው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነበር

ይበልጥ ድፍረት ማዳበር የሚያስፈልገኝ በየትኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ስመሠክር ነው?

  • በትምህርት ቤት

  • በሥራ ቦታ

  • ለቤተሰብ አባላት

  • በሌሎች ቦታዎች