በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ

ጥያቄ፦ ሁላችንም ማጽናኛ ማግኘት የሚያስፈልገን ጊዜ አለ። ታዲያ ማጽናኛ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

ጥቅስ፦ 2ቆሮ 1:3, 4

አበርክት፦ ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ እንዲህ ያለ ማጽናኛ የሚሰጠን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

መጠበቂያ ግንብ (የጀርባው ሽፋን)

ጥያቄ፦ አንዳንድ ሰዎች የአምላክ መንግሥት በልባችን ውስጥ ያለ ሁኔታ እንደሆነ ይሰማቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ ሰዎች ዓለም አቀፍ ሰላም ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት የሚገኝ ነገር እንደሆነ ያስባሉ። እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት?

ጥቅስ፦ ዳን 2:44

አበርክት፦ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ መንግሥት እውን መስተዳድር እንደሆነ ይናገራል። ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን መንግሥት አስመልክቶ የሚሰጠውን ተጨማሪ ሐሳብም ይዟል።

እውነትን አስተምሩ

ጥያቄ፦ አምላክ እንደሚያስብልን እንዴት ማወቅ እንችላለን?

ጥቅስ፦ 1ጴጥ 5:7

እውነታ፦ አምላክ ስለሚያስብልን ወደ እሱ እንድንጸልይ ጋብዞናል።

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።