በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል ውይይት መጀመር

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል ውይይት መጀመር

ኢየሱስ ከአንዲት ሳምራዊት ሴት ጋር ውይይት መጀመሩ መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲመሠክር አስችሎታል። ከማናውቃቸው ሰዎች ጋር ውይይት የመጀመር ክህሎታችንን ማሻሻል የምንችለው እንዴት ነው?

  • ተግባቢዎች ለመሆንና ከሰዎች ጋር ለመነጋገር ጥረት አድርጉ። ኢየሱስ ደክሞት የነበረ ቢሆንም የሚጠጣ ነገር በመጠየቅ ውይይት ጀምሯል። እናንተም ወዳጃዊ በሆነ መንፈስ ሰላምታ ከሰጣችሁ በኋላ ምናልባት ስለ አየሩ ጠባይ፣ ስለ አውቶቡሱ መዘግየት ወይም ወቅታዊ ስለሆነ ጉዳይ በማንሳት ውይይት ልትጀምሩ ትችላላችሁ። የመጀመሪያው ግባችሁ ከግለሰቡ ጋር ውይይት መጀመር መሆኑን አትዘንጉ፤ በመሆኑም የግለሰቡን ትኩረት ሊስብ የሚችል ማንኛውንም ርዕሰ ጉዳይ አንስታችሁ ተወያዩ። ለመወያየት ፈቃደኛ ባይሆን የምትከስሩት ነገር የለም። ከሌላ ሰው ጋር ውይይት ለመጀመር ጥረት ማድረጋችሁን ቀጥሉ። ይሖዋ ድፍረት እንዲሰጣችሁ ጠይቁት።—ነህ 2:4፤ ሥራ 4:29

  • ምሥራቹን መስበክ የምትችሉበትን አጋጣሚ በንቃት ተከታተሉ፤ ሆኖም አትቸኩሉ። ጭውውቱ በራሱ እንዲመራችሁ አድርጉ። አለዚያ ግለሰቡ ግራ ሊጋባና ውይይቱን ሊያቆም ይችላል። መመሥከር የምትችሉበት አጋጣሚ ሳታገኙ ውይይቱ ቢደመደም ተስፋ አትቁረጡ። መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥራቹን መስበክ የሚያስፈራችሁ ከሆነ የመመሥከር ግብ ሳትይዙ እንዲሁ ውይይት ለመጀመር ልምምድ አድርጉ። [ቪዲዮ 1⁠ን አጫውትና ተወያዩበት።]

  • ግለሰቡ ስለምታምኑበት ነገር ጥያቄ እንዲጠይቅ ሊያነሳሳ የሚችል ከልብ የመነጨ ሐሳብ ጣል በማድረግ ምሥክርነት መስጠት የምትችሉበት አጋጣሚ ለመፍጠር ሞክሩ። ኢየሱስ ሴትየዋ ጥያቄዎችን እንድትጠይቀው የሚያነሳሱ ትኩረት የሚስቡ ሐሳቦችን ተናግሮ ነበር። በኋላም ላነሳቻቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ምሥራቹን ነግሯታል። [ቪዲዮ 2⁠ን አጫውትና ተወያዩበት፤ ከዚያም ቪዲዮ 3⁠ን አጫውትና ተወያዩበት።]