ክርስቲያናዊ ሕይወት
ምንም አልባከነም
ኢየሱስ ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 5,000 ወንዶችን ተአምራዊ በሆነ መንገድ ከመገበ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ምንም እንዳይባክን የተረፈውን ቁርስራሽ ሁሉ ሰብስቡ” ሲል አዟቸዋል። (ዮሐ 6:12) ኢየሱስ ምንም ነገር እንዳይባክን በመጠንቀቅ ይሖዋ በልግስና ላቀረበው ነገር አድናቆት እንዳለው አሳይቷል።
በዘመናችንም የበላይ አካሉ በመዋጮ የተገኘውን ገንዘብ በጥበብ በመጠቀም የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ጥረት ያደርጋል። ለምሳሌ በዎርዊክ፣ ኒው ዮርክ የዋናው መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሲገነባ ወንድሞች ለሥራው የተመደበውን ገንዘብ ከሁሉ በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ንድፍ መርጠዋል።
በሚከተሉት ሁኔታዎች ሥር ብክነት እንዳይኖር መጠንቀቅ የምንችለው እንዴት ነው?
-
በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ ስንሆን
-
ለግል የምንጠቀምባቸውን ጽሑፎች ስንወስድ (km 5/09 3 አን. 4)
-
ለአገልግሎት የምንጠቀምባቸውን ጽሑፎች ስንወስድ (mwb17.02 “መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው” አን. 1)
-
አገልግሎት ላይ ስንሆን (mwb17.02 “መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው” አን. 2 እና ሣጥኑ