በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

ጥያቄዎችን ተጠቀሙ

ጥያቄዎችን ተጠቀሙ

“ደስተኛው አምላክ” ይሖዋ በአገልግሎታችን ደስታ እንድናገኝ ይፈልጋል። (1ጢሞ 1:11) ክህሎታችንን ለማሳደግ ጥረት ባደረግን መጠን ደስታችንም ይጨምራል። ጥያቄ መጠየቅ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ እንዲሁም በቀላሉ ውይይት ለመጀመር ያስችላል። ጥያቄዎች ሰዎች እንዲያስቡና እንዲያመዛዝኑ ለማድረግ ይረዳሉ። (ማቴ 22:41-45) ጥያቄ መጠየቃችንና ግለሰቡ መልስ ሲሰጥ ማዳመጣችን ለግለሰቡ ትልቅ ቦታ እንደምንሰጠው ያሳያል። (ያዕ 1:19) ግለሰቡ የሚሰጠው መልስ ውይይቱን እንዴት መቀጠል እንዳለብን ለመወሰን ሊረዳን ይችላል።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ጥያቄዎችን መጠቀም የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ጄድ የትኞቹን መልካም ባሕርያት አሳይታለች?

  • ኒታ ለጄድ ትኩረት እንደሰጠቻት ለማሳየት ጥያቄዎችን የተጠቀመችው እንዴት ነው?

  • ኒታ ጄድ ለምሥራቹ ፍላጎት እንዲኖራት ለመርዳት ጥያቄዎችን የተጠቀመችው እንዴት ነው?

  • ኒታ ጄድ እንድታስብና እንድታመዛዝን ለመርዳት ጥያቄዎችን የተጠቀመችው እንዴት ነው?