በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ

ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ

ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን በይሖዋ ዝግጅት ላይ በማመፅ ለእሱ ታማኝ አለመሆናቸውን አሳይተዋል። ይሖዋ ዓመፀኞቹንና ተባባሪዎቻቸውን በሙሉ አጥፍቷቸዋል። (ዘኁ 16:26, 27, 31-33) እኛስ ለይሖዋ ያለንን ታማኝነት የሚፈትን ምን ሁኔታ ሊያጋጥመን ይችላል? ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን እንዳንመስል የሚረዱን የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ናቸው?

ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ናዲያ ምን ፈታኝ ሁኔታ አጋጥሟታል? ታማኝ እንድትሆን የረዳትስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

  • ተገቢ ያልሆነ ነገር እንደተፈጸመ የተሰማው አንድ ወንድም የተፈተነው እንዴት ነው? ታማኝ እንዲሆን የረዳውስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

  • ቴረንስ ምን ፈታኝ ሁኔታ አጋጥሞታል? ታማኝ እንዲሆን የረዳውስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

  • አንድ ወንድም በትምህርት ቤት ምን ፈታኝ ሁኔታ አጋጥሞታል? ታማኝ እንዲሆን የረዳውስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?