ከመጋቢት 8-14
ዘኁልቁ 9-10
መዝሙር 31 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ይሖዋ ሕዝቡን የሚመራው እንዴት ነው?”፦ (10 ደቂቃ)
መንፈሳዊ ዕንቁዎች፦ (10 ደቂቃ)
ዘኁ 9:13—ክርስቲያኖች ለእስራኤላውያን ከተሰጠው ከዚህ መመሪያ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ? (it-1 199 አን. 3)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ) ዘኁ 10:17-36 (th ጥናት 5)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ፦ (3 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ጀምር። የቤቱ ባለቤት ፍላጎት ካሳየ በኋላ የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።) (th ጥናት 11)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ) ቀደም ሲል መሥክረህለት የነበረ የሥራ ባልደረባህን ወይም አብሮህ የሚማርን ልጅ ወደ መታሰቢያው በዓል ጋብዝ። (th ጥናት 2)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (5 ደቂቃ) bhs 214 ተጨማሪ ሐሳብ 16—ጥናትህን ወደ መታሰቢያው በዓል ጋብዝ፤ እንዲሁም ከቂጣውና ከወይን ጠጁ መካፈል የሌለበት ለምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅመህ አስረዳው። (th ጥናት 17)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
የስብከቱን ሥራ ለመደገፍ በቤቴል የተደረጉ ማስተካከያዎች፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ በ2015 ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ምን ማስታወቂያ ተነግሮ ነበር? ለውጡ የተደረገው በየትኞቹ ሁለት ምክንያቶች የተነሳ ነው? በቤቴል ምን ማስተካከያዎች ተደርገዋል? ማስተካከያዎቹስ ምን ጥቅም አስገኝተዋል? ማስታወቂያው በብሪታንያ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ምን ለውጥ እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል? እነዚህ ማስተካከያዎች ይሖዋ እየመራን እንዳለ የሚያረጋግጡት እንዴት ነው?
ቤቴልን የጎበኘነው ለምንድን ነው? (5 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) rr ምዕ. 6 አን. 1-6፣ ማስተዋወቂያ ቪዲዮ
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 12 እና ጸሎት