ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ውጥረት ውስጥ ብትሆኑም የዋህነት አሳዩ
ሙሴ ውጥረትና ጫና ባጋጠመው ወቅት የዋህነቱ ተፈትኖ ነበር (ዘኁ 20:2-5፤ w19.02 12 አን. 19)
ሙሴ ለተወሰነ ጊዜ ያህል የዋህነት ሳያሳይ ቀርቷል (ዘኁ 20:10፤ w19.02 13 አን. 20-21)
ሙሴና አሮን ለሠሩት ከባድ ስህተት ይሖዋ ተግሣጽ ሰጥቷቸዋል (ዘኁ 20:12፤ w09 9/1 19 አን. 5)
የዋህ የሆነ ሰው በቀላሉ አይበሳጭም፤ እንዲሁም ኩሩ ወይም ትዕቢተኛ አይደለም። የዋህነት የሚጎዳ ነገር ቢያጋጥመንም ሳንበሳጭ፣ ቂም ሳንይዝና ለበቀል ሳንነሳሳ ሁኔታውን በትዕግሥት እንድንወጣው ያስችለናል።