በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

የአምላክን ቃል ተጠቀሙ

የአምላክን ቃል ተጠቀሙ

የአምላክ ቃል ኃይል አለው! (ዕብ 4:12) አምላክን የማያውቁ ሰዎችን ልብ እንኳ መንካት ይችላል። (1ተሰ 1:9፤ 2:13) አንድ ሰው ላሳየነው አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አድናቆት ሲያድርበት መመልከት እኛንም በእጅጉ ያስደስተናል።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል መጠቀም የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ኒታ ጥቅሱን ስታስተዋውቅ የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል የተጠቀመችበት እንዴት ነው?

  • ኒታ ጥቅሱን ስታስነብብና ስታወያይ የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል የተጠቀመችበት እንዴት ነው?

  • ጥቅሱ የጄድን ልብ እንደነካው የሚጠቁመው ምንድን ነው? ይህስ በኒታ ላይ ምን ስሜት ያሳደረባት ይመስልሃል?