በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጓደኞቻችሁን በጥበብ ምረጡ

ጓደኞቻችሁን በጥበብ ምረጡ

እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሳሉ የደረሰባቸው ነገር ለክርስቲያኖች የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ይሆናል። (1ቆሮ 10:6, 8, 11) የፆታ ብልግና ከሚፈጽሙትና ጣዖት አምላኪ ከሆኑት የሞዓብ ሴቶች ጋር የተቀራረቡት እስራኤላውያን ተታለው ከባድ ኃጢአት ፈጽመዋል። ይህም አስከፊ መዘዝ አስከትሏል። (ዘኁ 25:9) እኛም በዙሪያችን ያሉት ሰዎች ማለትም የሥራ ባልደረቦቻችን፣ አብረውን የሚማሩት ልጆች፣ ዘመዶቻችን እንዲሁም ሌሎች የምናውቃቸው ሰዎች ይሖዋን አያመልኩም። እንዲህ ካሉ ሰዎች ጋር የቅርብ ወዳጅነት መመሥረት ስላለው አደጋ ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ዚምሪ እና ሌሎቹ ሰዎች ለያሚን የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚንጸባረቅበት ምን ነገር ነግረውታል?

  • ፊንሃስ፣ ያሚን ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖረው የረዳው እንዴት ነው?

  • ለማያምኑ ሰዎች ወዳጃዊ ስሜት በማሳየትና የእነሱ ጓደኛ በመሆን መካከል ምን ልዩነት አለ?

  • በጉባኤ ውስጥም የቅርብ ጓደኞች በምንመርጥበት ጊዜ ጠንቃቆች መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

  • ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በግል የማናውቃቸው ሰዎች በሚገኙባቸው የቻት ቡድኖች ውስጥ ከመግባት መቆጠብ ያለብን ለምንድን ነው?