በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ መጥፎ ልማዶችን እንዲያስወግዱ እርዷቸው
ከይሖዋ ጋር ጥሩ ዝምድና የሚኖራቸው ንጹሕ ሥነ ምግባር ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው። (1ጴጥ 1:14-16) በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች መጥፎ ልማዶችን ማስወገዳቸው የቤተሰብ ሕይወታቸውንና ጤንነታቸውን ያሻሽልላቸዋል፤ ከገንዘብ ጋር በተያያዘም ጥቅም ያስገኝላቸዋል።
የይሖዋ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ምን እንደሆኑ፣ ይሖዋ እነዚህን መሥፈርቶች ያወጣበትን ምክንያትና እነሱን መከተል የሚያስገኘውን ጥቅም በግልጽ አስረዷቸው። ጥናቶቻችሁ የሚያስቡበትን መንገድ እንዲለውጡ በመርዳት ላይ አተኩሩ፤ የሚያስቡበት መንገድ ከተለወጠ ድርጊታቸውም መለወጡ አይቀርም። (ኤፌ 4:22-24) ሥር የሰደዱ መጥፎ ልማዶችን በይሖዋ እርዳታ ማሸነፍ እንደሚችሉ አረጋግጡላቸው። (ፊልጵ 4:13) ኃጢአት ለመሥራት ሲፈተኑ ወደ ይሖዋ እንዲጸልዩ አስተምሯቸው። ፈታኝ ሁኔታዎችን ለይተው ማወቅና ከእነዚህ ሁኔታዎች መራቅ እንዲችሉ እርዷቸው። መጥፎ ልማዶችን ጤናማ በሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዲተኩ አበረታቷቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በይሖዋ እርዳታ ለውጥ ሲያደርጉ ማየት በጣም ያስደስታል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ መጥፎ ልማዶችን እንዲያስወግዱ እርዷቸው የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ሽማግሌዎቹና ኒታ፣ ጄድን እንደሚተማመኑባት ያሳዩት እንዴት ነው?
-
ኒታ ለጄድ ተጨማሪ እርዳታ የሰጠቻት እንዴት ነው?
-
ጄድ የይሖዋን እርዳታ ለማግኘት ጥረት ያደረገችው እንዴት ነው?