ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
እብሪት ለውርደት ይዳርጋል
ንጉሥ ሳኦል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ተሰምቶት ነበር (1ሳሙ 13:5-7)
ሳኦል ልኩን በማወቅ የይሖዋን መመሪያ ከመቀበል ይልቅ የእብሪት እርምጃ ወስዷል (1ሳሙ 13:8, 9፤ w00 8/1 13 አን. 17)
ይሖዋ ሳኦልን ቀጥቶታል (1ሳሙ 13:13, 14፤ w07 6/15 27 አን. 8)
እብሪተኛ የሆነ ሰው በችኮላ ወይም በሞኝነት፣ ያልተፈቀደለትን ነገር ያደርጋል። እብሪት፣ ልክን የማወቅ ተቃራኒ ነው። አንድ ሰው የእብሪት እርምጃ እንዲወስድ ሊፈትኑት የሚችሉት የትኞቹ ሁኔታዎች ናቸው?