በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ከይሖዋ ጋር የግል ዝምድና እንዲመሠርቱ እርዷቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ከይሖዋ ጋር የግል ዝምድና እንዲመሠርቱ እርዷቸው

ይሖዋ በፍቅር ተነሳስተን እንድናገለግለው ይፈልጋል። (ማቴ 22:37, 38) የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች አስፈላጊውን ለውጥ እንዲያደርጉና ፈተናዎችን በጽናት እንዲቋቋሙ የሚረዳቸው ለአምላክ ያላቸው ፍቅር ነው። (1ዮሐ 5:3) ለመጠመቅ የሚገፋፋቸውም ለአምላክ ያላቸው ፍቅር ነው።

ጥናቶቻችሁ አምላክ እንደሚወዳቸው እንዲገነዘቡ እርዷቸው። “ይህ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምርሃል?” ወይም “ይህ አምላክ ለአንተ ያለውን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው?” እንደሚሉት ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቋቸው። ይሖዋ እነሱን በግለሰብ ደረጃ እየረዳቸው ያለው እንዴት እንደሆነ እንዲያስተውሉ እርዷቸው። (2ዜና 16:9) ይሖዋ ለጸሎታችሁ መልስ የሰጣችሁ እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን ንገሯቸው፤ እንዲሁም እነሱ የሚያቀርቡትን ጸሎት የሚመልስላቸው እንዴት እንደሆነ እንዲያስተውሉ አበረታቷቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ይሖዋ ላሳያቸው ፍቅር ምላሽ ሲሰጡና ከእሱ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት ሲመሠርቱ ማየት በጣም ያስደስታል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ከይሖዋ ጋር የግል ዝምድና እንዲመሠርቱ እርዷቸው የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ጄድ ምን ፈተና አጋጥሟት ነበር?

  • ኒታ ጄድን የረዳቻት እንዴት ነው?

  • ጄድ ያጋጠማትን ፈተና መወጣት የቻለችው እንዴት ነው?