ክርስቲያናዊ ሕይወት
የኢንተርኔት ጓደኞችህ እነማን ናቸው?
“ጓደኛ” የሚለው ቃል “በፍቅር ወይም በአክብሮት ተነሳስተን የምንቀርበው ሰው” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። ለምሳሌ ያህል፣ በዮናታን እና በዳዊት መካከል የማይበጠስ ወዳጅነት የተመሠረተው ዳዊት ጎልያድን ከገደለው በኋላ ነው። (1ሳሙ 18:1) ሁለቱም ሰዎች፣ አንዳቸውን በሌላው ዘንድ ተወዳጅ የሚያደርጋቸው ባሕርይ ነበራቸው። ስለዚህ የጠንካራ ወዳጅነት መሠረቱ ትክክለኛ እውቀት ነው። በጥቅሉ ሲታይ፣ አንድን ሰው ማወቅ ጊዜና ጥረት ይጠይቃል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ግን ሰዎች አንዲት ቁልፍ በመጫን ብቻ “ጓደኞች” መሆን ይችላሉ። ኢንተርኔት ላይ የምናገኛቸው ሰዎች፣ የሚናገሩትን ነገር በጥንቃቄ ማቀድና ሌሎች ለእነሱ የሚኖራቸውን አመለካከት በተወሰነ መጠን መቆጣጠር የሚችሉበት አጋጣሚ አላቸው፤ ይህም እውነተኛ ማንነታቸውን መደበቅ ቀላል እንዲሆንላቸው ያደርጋል። በመሆኑም በኢንተርኔት አማካኝነት ጓደኝነት ከመመሥረት ጋር በተያያዘ የምንመራበት መርሕ ሊኖረን ይገባል። ‘ስሜታቸውን ልጎዳው እችላለሁ’ ብላችሁ በማሰብ በደንብ የማታውቋቸው ሰዎች የሚያቀርቡላችሁን የጓደኝነት ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ አትፍሩ። አንዳንዶች ማኅበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም ያለውን አደጋ በመገንዘብ ጨርሶ ላለመጠቀም ወስነዋል። ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለመጠቀም ከወሰናችሁ ግን ምን ነገሮችን ማስታወስ ይኖርባችኋል?
ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
አንድ ነገር ከመጻፍህ ወይም ፎቶዎችን ከመለጠፍህ በፊት ምን ነገሮችን ማስታወስ ይኖርብሃል?
-
ኢንተርኔት ላይ ጓደኛ የምታደርጋቸውን ሰዎች በጥንቃቄ መምረጥ ያለብህ ለምንድን ነው?
-
ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም በምታሳልፈው ጊዜ ላይ ገደብ ማበጀት ያለብህ ለምንድን ነው?—ኤፌ 5:15, 16