ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
አንድ አባት ለልጁ የሰጠው ፍቅራዊ ምክር
ከይሖዋ ጋር በግለሰብ ደረጃ ወዳጅነት መሥርት (1ዜና 28:9፤ w05 2/15 19 አን. 9)
ይሖዋን በሙሉ ልብህ አገልግለው (1ዜና 28:9፤ w12 4/15 16 አን. 13)
በይሖዋ ታመን፤ አትፍራ (1ዜና 28:20፤ w17.09 32 አን. 20-21)
በዕድሜ የገፋው ንጉሥ ዳዊት፣ ወጣትና ተሞክሮ የሌለው ልጁ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን የመገንባቱን ትልቅ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ይህን ምክር ሰጥቶታል። ይህ ምክር ለሁላችንም በተለይም ለወጣት ክርስቲያኖች ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?