ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ንጉሥ ሰለሞን ጥበብ የጎደለው ውሳኔ አደረገ
[የ2 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ሰለሞን ብዙ ፈረሶችንና ሠረገሎችን ከግብፅ አስመጣ (ዘዳ 17:15, 16፤ 2ዜና 1:14, 17)
በሰለሞን የጦር ኃይል ውስጥ የተካተቱት እነዚህ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚቀመጡባቸው ከተሞች እንዲሁም እነሱን የሚንከባከቧቸው ሰዎች ያስፈልጉ ነበር (2ዜና 1:14፤ it-1 174 አን. 5፤ 427)
በሰለሞን ግዛት አብዛኛው ክፍል ሕዝቡ ተመችቷቸው ይኖሩ የነበረ ቢሆንም በንጉሥ ሮብዓም ዘመን ዓመፁ። ምክንያቱም ሮብዓም፣ አባቱ የጫነባቸውን ሸክም ከማቅለል ይልቅ አክብዶባቸው ነበር። (2ዜና 10:3, 4, 14, 16) ምንጊዜም ቢሆን የምናደርጋቸው ውሳኔዎች የሚያስከትሉት ውጤት አለ።—ገላ 6:7