በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

‘ልባችሁን ጠብቁ’

‘ልባችሁን ጠብቁ’

ሰለሞን በመንፈስ ተመርቶ “ከምንም ነገር በላይ ልብህን ጠብቅ” በማለት ጽፏል። (ምሳሌ 4:23) የሚያሳዝነው፣ የአምላክ ሕዝቦች የሆኑት እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት “በሙሉ ልባቸው” መመላለሳቸውን አቁመዋል። (2ዜና 6:14) ንጉሥ ሰለሞን እንኳ ጣዖት አምላኪ የሆኑት ሚስቶቹ፣ ልቡ ሌሎች አማልክትን ወደ መከተል እንዲያዘነብል እንዲያደርጉት ፈቅዷል። (1ነገ 11:4) እናንተስ ልባችሁን መጠበቅ የምትችሉት እንዴት ነው? በጥር 2019 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 14-19 ላይ የወጣው የጥናት ርዕስ ስለዚህ ጉዳይ ይናገራል።

ከመጠበቂያ ግንብ የምናገኛቸው ትምህርቶች—ልብህን ጠብቅ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

የሚከተሉት ክርስቲያኖች እምነታቸውን ሊያዳክም የሚችል ምን ተጽዕኖ አጋጥሟቸዋል? ይህ የጥናት ርዕስ ልባቸውን ለመጠበቅ የረዳቸውስ እንዴት ነው?

  • ብሬንት እና ሎረን

  • ኡምጄይ

  • ሃፒ ላዩ

ይህ የጥናት ርዕስ እናንተንስ የረዳችሁ እንዴት ነው?