በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ልቤ ሁልጊዜ በዚያ ይሆናል”

“ልቤ ሁልጊዜ በዚያ ይሆናል”

ይሖዋ ቤተ መቅደሱን ለራሱ መርጦታል (2ዜና 7:11, 12)

ይሖዋ ልቡ ሁልጊዜ በዚያ እንደሚሆን ተናግሯል፤ ይህም ስሙ በሚጠራበት በዚህ ቤት ውስጥ የሚከናወነውን ነገር በትኩረት እንደሚከታተል ያመለክታል (2ዜና 7:16w02 11/15 5 አን. 1)

ይሖዋ፣ ሕዝቡ በፊቱ “በሙሉ ልባቸው” መመላለሳቸውን ካቆሙ ቤተ መቅደሱ እንዲጠፋ ይፈቅዳል (2ዜና 6:14፤ 7:19-21it-2 1077-1078)

ቤተ መቅደሱ በተመረቀበት ወቅት ሕዝቡ ልባቸው ሁልጊዜ በቤተ መቅደሱ እንደሚሆን አስበው መሆን አለበት። የሚያሳዝነው ግን ሕዝቡ ቀስ በቀስ ለይሖዋ አምልኮ ያላቸው ቅንዓት እየቀዘቀዘ መጣ።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦  ‘በሙሉ ልብ አምልኮ እንደማቀርብ እያሳየሁ ያለሁት እንዴት ነው?’