በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ ጥበብ ለማግኘት ይረዳል

መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ ጥበብ ለማግኘት ይረዳል

አምላካዊ ጥበብ እንደተሸሸገ ሀብት ውድ ነው። (ምሳሌ 2:1-6) ጥበብ፣ አስተዋዮች እንድንሆንና ጥሩ ውሳኔ እንድናደርግ ይረዳናል። ከጉዳትም ይጠብቀናል። በመሆኑም ጥበብ “በጣም አስፈላጊ ነገር” ነው። (ምሳሌ 4:5-7) በአምላክ ቃል ውስጥ የተሸሸገውን መንፈሳዊ ሀብት ቆፍሮ ለማውጣት ጥረት ይጠይቃል። የአምላክን ቃል “ቀንም ሆነ ሌሊት” ማለትም በየዕለቱ በማንበብ መጀመር እንችላለን። (ኢያሱ 1:8) የአምላክን ቃል አዘውትረን ለማንበብና ከንባባችን ደስታ ለማግኘት የሚረዱንን አንዳንድ ነገሮች እስቲ እንመልከት።

ወጣቶች የአምላክን ቃል መውደድ የተማሩት እንዴት ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

እነዚህ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ለማንበብ ጥረት ሲያደርጉ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሟቸዋል? የረዳቸውስ ምንድን ነው?

  • ሜላኒ

  • ሳሙኤል

  • ሴሊን

  • ራፌሊዮ

መጽሐፍ ቅዱስን የማነብበት ፕሮግራም፦