በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጽሐፍ ቅዱስን ከማስጠናት ጋር የተያያዙ ቪዲዮዎችን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ከማስጠናት ጋር የተያያዙ ቪዲዮዎችን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

በአገልግሎት ላይ የምንጠቀምባቸው መጽሐፍ ቅዱስን ከማስጠናት ጋር የተያያዙ አራት ቪዲዮዎች አሉን። እያንዳንዱ ቪዲዮ የተዘጋጀበት ዓላማ ምንድን ነው?

  • መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?—ሙሉው ቪዲዮ የተዘጋጀው የተለያየ ሃይማኖታዊ እምነት ያላቸው ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለማወቅ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ታስቦ ነው። ሰዎች ለሚፈጠሩባቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘወር እንዲሉ ያበረታታል፤ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምክንያታዊ የሆነ መረጃ እንደሚገኝ የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስጠናቸው ሰው ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉም ያብራራል።

  • መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? (አጭሩ) ከሙሉው ቪዲዮ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ቢኖረውም ርዝመቱ የሙሉውን ቪዲዮ አንድ ሦስተኛ ያክላል። ረጅም ሰዓት ለመወያየት ጊዜ የሌላቸው ሰዎች ባሉባቸው ክልሎች ውስጥ ይህ ቪዲዮ ይበልጥ ውጤታማ ሊሆን ይችላል።

  • መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተዘጋጀው ሰዎች ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ለማጥናት ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማድረግ፣ ከዚህ ዝግጅት ጋር በተያያዘ የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስጠናቸው ሰው ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለማብራራት ታስቦ ነው።

  • ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራምህ እንኳን ደህና መጣህ የተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንዲያዩት ታስቦ ነው። ቪዲዮው የሚተዋወቀው ለዘላለም በደስታ ኑር! በተባለው መጽሐፍ ገጽ ሁለት ላይ ቢሆንም ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅመን ሰዎችን በምናወያይበት ጊዜም ልናሳየው እንችላለን። ቪዲዮው የመጽሐፉን ይዘት እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ምን እንደሚመስል ያብራራል።

እያንዳንዱ ቪዲዮ የተዘጋጀበት የራሱ የሆነ ዓላማ ቢኖረውም ተገቢ መስሎ በታየን ጊዜ ሁሉ የትኛውንም ቪዲዮ ማሳየት ወይም መላክ እንችላለን። አስፋፊዎች ከእነዚህ ቪዲዮዎች ጋር በደንብ መተዋወቃቸው እንዲሁም ቪዲዮዎቹን በአገልግሎት ላይ ጥሩ አድርገው መጠቀማቸው አስፈላጊ ነው።