በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመጋቢት 17-23

ምሳሌ 5

ከመጋቢት 17-23

መዝሙር 122 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ከፆታ ብልግና ራቁ

(10 ደቂቃ)

የፆታ ብልግና አጓጊ ሊመስል ይችላል (ምሳሌ 5:3w00 7/15 29 አን. 2)

የፆታ ብልግና መራራ ውጤት ያስከትላል (ምሳሌ 5:4, 5w00 7/15 29 አን. 3)

ከፆታ ብልግና ራቁ (ምሳሌ 5:8w00 7/15 29 አን. 6)

አንዲት እህት ለአንድ ልጅ ስልክ ቁጥሯን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗን ስትገልጽ

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 5:9—የፆታ ብልግና ‘ክብራችንን ለሌሎች አሳልፈን እንድንሰጥ’ የሚያደርገን እንዴት ነው? (w00 7/15 29 አን. 8)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የክርስትና እምነት ተከታይ ያልሆነን ሰው በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ ጋብዝ፤ እንዲሁም jw.org​ን ተጠቅመህ በዓሉ እሱ በሚኖርበት አካባቢ የሚከበርበትን ቦታ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 6 ነጥብ 4)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ግለሰቡ የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ወስዷል፤ እንዲሁም ፍላጎት እንዳለው አሳይቷል። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 16 ማጠቃለያ፣ ክለሳ እና ግብ። ተማሪው የኢየሱስ መልክ ምን ይመስል እንደነበር ሲጠይቅህ ምርምር አድርጎ መልሱን ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 121

7. በምትጠናኑበት ጊዜ የሥነ ምግባር ንጽሕናችሁን ለመጠበቅ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ውሰዱ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

በጥቅሉ ሲታይ መጠናናት የሚባለው አንዳቸው ለሌላው የፍቅር ስሜት ያላቸው ሁለት ሰዎች አብረው የሚያሳልፉት ጊዜ ነው። ሁለት ሰዎች ብቻቸውን ወይም ሌሎች ሰዎች ባሉበት፣ በሚስጥር ወይም በይፋ እንዲሁም በአካል፣ በስልክ ወይም በጽሑፍ መልእክት አማካኝነት ሊጠናኑ ይችላሉ። መጠናናት እንዲሁ ለመዝናናት ተብሎ የሚደረግ ነገር ሳይሆን ወደ ትዳር ሊያመራ የሚችል ትልቅ እርምጃ መሆኑን እንገነዘባለን። ወጣቶችም ሆኑ ትላልቅ ሰዎች በሚጠናኑበት ጊዜ ከፆታ ብልግና እንዲጠበቁ የትኞቹን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ይችላሉ?—ምሳሌ 22:3

ለጋብቻ መዘጋጀት—ክፍል 1፦ የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ ደርሻለሁ? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • አንድ ሰው ለጋብቻ ዝግጁ እስኪሆን ድረስ የፍቅር ጓደኛ መያዝ የሌለበት ለምንድን ነው? (ምሳሌ 13:12፤ ሉቃስ 14:28-30)

  • በቪዲዮው ላይ የታዩት ወላጆች ልጃቸውን ከረዱበት መንገድ ትኩረታችሁን የሳበው ምንድን ነው?

ምሳሌ 28:26ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • የሚጠናኑ ጥንዶች ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ሥር ብቻቸውን እንዳይሆኑ አስቀድመው ዕቅድ ማውጣት የሚችሉት እንዴት ነው?

  • የሚጠናኑ ጥንዶች እጅ ለእጅ እንደ መያያዝና እንደ መሳሳም ካሉ የፍቅር መግለጫዎች ጋር በተያያዘ አስቀድመው ግልጽ ገደብ ማውጣታቸው የጥበብ እርምጃ የሆነው ለምንድን ነው?

ኤፌሶን 5:3, 4ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • የሚጠናኑ ጥንዶች በስልክ ወይም በኢንተርኔት አማካኝነት ከሚያደርጉት ጭውውት ጋር በተያያዘ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 24 አን. 1-6

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 3 እና ጸሎት