ከሚያዝያ 21-27
ምሳሌ 10
መዝሙር 76 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. እውነተኛ ብልጽግና የሚያስገኘው ምንድን ነው?
(10 ደቂቃ)
ብልጽግና በመንፈሳዊው የመከር ሥራ ተግቶ መሥራትን ያካትታል (ምሳሌ 10:4, 5፤ w01 7/15 25 አን. 1-3)
ጽድቅ ከቁሳዊ ብልጽግና የበለጠ ዋጋ አለው (ምሳሌ 10:15, 16፤ w01 9/15 24 አን. 3-4)
እውነተኛ ብልጽግና የሚገኘው በይሖዋ በረከት ነው (ምሳሌ 10:22፤ it-1 340)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
ምሳሌ 10:22—የይሖዋ በረከት ሥቃይን የማይጨምር ከሆነ የአምላክ አገልጋዮች ብዙ ፈተናዎችን የሚጋፈጡት ለምንድን ነው? (w06 5/15 30 አን. 18)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 10:1-19 (th ጥናት 10)
4. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ በአምላክ እንደማያምን ይነግርሃል። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)
5. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 4)
6. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ ትኩረቱን ሊስብ የሚችል መረጃ ከjw.org ላይ እንዴት ማግኘት እንደሚችል አሳየው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)
መዝሙር 111
7. የአምላክ አገልጋዮችን ባለጸጋ የሚያደርጓቸው የትኞቹ በረከቶች ናቸው?
(7 ደቂቃ) ውይይት።
ይሖዋ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ለአገልጋዮቹ የሚያፈስላቸው በረከት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመቋቋም አልፎ ተርፎም እውነተኛ ብልጽግና ለማግኘት ይረዳቸዋል። (መዝ 4:3፤ ምሳሌ 10:22) የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ከዚያም የይሖዋ በረከት ባለጸጋ የሚያደርገን እንዴት እንደሆነ አድማጮችን ጠይቅ።
አንዳንዶች አገልግሎታቸውን በማስፋት መንፈሳዊ ብልጽግናቸውን ማሳደግ ችለዋል።
ወጣቶች—ወደ ሰላም የሚወስደውን ጎዳና ምረጡ! የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
-
ከሃርሊ፣ ከአንጂል እና ከካርሊ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
8. የ2025 የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ፕሮግራም ሪፖርት
(8 ደቂቃ) ንግግር። ቪዲዮውን አጫውት።
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 25 አን. 8-13፣ በገጽ 201 ላይ ያለው ሣጥን