በጀርመን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ሲከበር

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ መጋቢት 2016

የአቀራረብ ናሙናዎች

ለመጠበቂያ ግንብ መጽሔትና ለ2016 የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል የመጋበዣ ወረቀት የተዘጋጁ የአቀራረብ ናሙናዎች፤ ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን የአቀራረብ ናሙና አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ በመቆርቆር እርምጃ ወስዳለች

አስቴር አይሁዳውያንን ከጥፋት ለመታደግ በድፍረት ሕይወቷን አደጋ ላይ ጥላ መርዶክዮስ አዲስ ሕግ እንዲያረቅ ረድታዋለች። (አስቴር 6-10)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—መጽሔት ለማበርከት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔትን ለማበርከት የሚረዱ መግቢያዎችን ለማዘጋጀት የሚያግዙ ሐሳቦችን ተጠቀምባቸው

ክርስቲያናዊ ሕይወት

እንግዶቻችንን መቀበል

እንግዶችንና የቀዘቀዙ ሰዎችን ሞቅ ባለ ስሜት መቀበል የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢዮብ በመከራ ውስጥ ንጹሕ አቋሙን ጠብቋል

ኢዮብ በሕይወት ውስጥ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ለይሖዋ መሆኑን አሳይቷል። (ኢዮብ 1-5)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ታማኙ ኢዮብ ሥቃይ እንደበዛበት ተናገረ

ኢዮብ ያጋጠመው ከፍተኛ ሐዘንና የተሰማው የተስፋ መቁረጥ ስሜት በአመለካከቱ ላይ ተጽዕኖ ያደረገበት ቢሆንም ለይሖዋ አምላክ ያለው ፍቅር ግን አልተለወጠም። (ኢዮብ 6-10)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢዮብ በትንሣኤ ተስፋ ላይ እምነት ነበረው

ኢዮብ፣ አንድ ጎቶ እንደገና ከሥሩ እንደሚያቆጠቁጥ ሁሉ አምላክም እሱን ከሞት እንደሚያስነሳው ያውቅ ነበር። (ኢዮብ 11-15)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ትንሣኤ—በቤዛው አማካኝነት የተገኘ ስጦታ

ይሖዋ ያዘጋጀው የቤዛው ስጦታ በትንሣኤ ተስፋ ላይ ያለንን እምነት አረጋግጦልናል። በምንወዳቸው ዘመዶቻችንን ከማልቀስ ይልቅ ከሞት ሲነሱ እንቀበላቸዋለን።