በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዮብ 1-5

ኢዮብ በመከራ ውስጥ ንጹሕ አቋሙን ጠብቋል

ኢዮብ በመከራ ውስጥ ንጹሕ አቋሙን ጠብቋል

ኢዮብ እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነፃ በወጡበት ወቅት በዖጽ ምድር ይኖር ነበር። ኢዮብ እስራኤላዊ ባይሆንም ይሖዋን በታማኝነት ያመልክ ነበር። ኢዮብ ሰፊ ቤተሰብ ያለው፣ እጅግ ባለጸጋና በሚኖርበት አካባቢ ተሰሚነት የነበረው ሰው ነው። የተከበረ አማካሪና የማያዳላ ዳኛ ነበር። ለድሆችና ችግር ላይ ለወደቁ ሰዎች ለጋስ ነበር። ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን የሚጠብቅ ሰው ነበር።

ኢዮብ በሕይወቱ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለይሖዋ እንደሆነ በማያሻማ መንገድ አሳይቷል

1:8-11, 22፤ 2:2-5

  • ሰይጣን ኢዮብ ንጹሕ አቋም እንዳለው ተመልክቷል። ኢዮብ ይሖዋን እንደሚታዘዝ አልካደም፤ ከዚህ ይልቅ ኢዮብ ይህን ለማድረግ የተነሳሳበት ዓላማ ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል

  • ሰይጣን ‘ኢዮብ ይሖዋን የሚያገለግለው በራስ ወዳድነት ተነሳስቶ ነው’ ብሏል

  • ለቀረበው ክስ መልስ ለማስገኘት ሰይጣን በዚህ ታማኝ ሰው ላይ ጥቃት እንዲያደርስ ይሖዋ ፈቅዷል። ሰይጣን የኢዮብን ሕይወት ሙሉ በሙሉ አመሰቃቀለበት

  • ኢዮብ ንጹሕ አቋም እንዳለው ቢያረጋግጥም ሰይጣን በመላው የሰው ልጆች ንጹሕ አቋም ጠባቂነት ላይ ጥያቄ አስነሳ

  • ኢዮብ ኃጢአት አልሠራም ወይም አምላክን በደል ሠርቷል ብሎ አልወነጀለም